-
サマリー
あらすじ・解説
የትግራይ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ከፍተኛ የትግራይ ወታደራዊ መኮንኖች የሰጡትን መግለጫ እና የያዙት አቋም “በመደገፍም ሆነ በመቃወም” ሰልፍ ማካሔድ እንደማይቻል አስታወቀ። ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል 100 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ለታንዛኒያ የምትሸጥበት ሥምምነት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። በሱዳን ዳርፉር ግዛት ኤል-ፋሽር በሚገኝ ሆስፒታል ላይ በሰው አልባ አውሮፕላን በተፈጸመ ጥቃት 30 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ። ሦስት የደቡብ አፍሪካ ሰላም አስከባሪዎች በዴሞክራቲት ሪፐብሊክ ኮንጎ ተገደሉ። በጋዛ የተኩስ አቁም ሥምምነት መሠረት እስራኤል 200 ፍልስጤማውያን እስረኞችን፤ ሐማስ 4 ታጋቾችን ዛለቀቁ።
activate_buybox_copy_target_t1