エピソード

  • DW Amharic የሚያዝያ 12 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/20
    በዓለም ዙሪያ የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓልን አከበሩ። ሩሲያ እና ዩክሬን የተኩስ አቁም በመጣስ እርስ በርስ ተወነጃጀሉ። የእስራኤል ጦር በጋዛ 15 የሕክምና ባለሙያዎች የተገደሉበት ባለፈው ወር የተፈጸመ ጥቃት ላይ በተደረገ ምርመራ በርካታ ሙያዊ ስሕተቶች እና የትዕዛዝ ጥሰቶች መገኘታቸውን ይፋ አደረገ። ከፍራንክፉርት አቅራቢያ ሁለት ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የጀርመን ፖሊስ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከፍተኛ ዘመቻ እያካሔደ ነው። በሺሕዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ እና ፖሊሲዎቻቸውን በመቃወም ኒው ዮርክ እና ዋሽንግተንን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች አደባባይ ወጡ።
    続きを読む 一部表示
    8 分
  • የሚያዝያ 11 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/19
    የኢትዮጵያ የጸጥታ አስከባሪዎች በአዲስ ስታንዳርድ ሚዲያ ቢሮ እና በተቋሙ ሠራተኛ የመኖሪያ ቤት ብርበራ ማካሔዳቸውን ጃኬን አሳታሚ አስታወቀ። ፍሬድሪሽ ሜርስ የጀርመንን ኢኮኖሚ ለማዘመን ቃል ገቡ። የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ፋሲካን ምክንያት በማድረግ በዩክሬን በሚካሔደው ጦርነት በተናጠል ተኩስ አቁም አወጁ። የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ግን የሩሲያው ፕሬዝደንት "በሰዎች ሕይወት ለመጫወት እየሞከሩ ነው" ሲሉ በታወጀው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም እምነት እንደሌላቸው የሚጠቁም አስተያየት ሰጥተዋል። ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች።
    続きを読む 一部表示
    9 分
  • የሚያዚያ 10 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/18
    -በመላዉ ዓለም የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዛሬ የሥቅለት በዓልን አክብረዉ ዋሉ።በአሉ ቫቲካን ዉስጥ በርዕሰ ሊቃነ-ጳጳሳቱ ሕመም፣ እየሩሳሌም ዉስጥ በጦርነት መሐል ግን የግሪጎሪያንና የዩሊዮስ የቀን አቀጣጠርን በሚከተለዉ ዓለም ሁሉ አንድ ቀን ተከብሯል።----የእስራኤል ጦር ጋዛ ሠርጥ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ደግሞ የመን ዉስጥ በርካታ ሰዎችን ገደሉ።እስራኤል ታጋቾች እንዲለቀቁ ያቀረበችዉን ጥያቄ ሐማስ ዉድቅ አደረገዉ።---የዩክሬንና የሩሲያን ጦርነትን በድርድር ለማስቆም ዩናይትድ ስቴትስ የምታደርገዉ ጥረት ባጭር ጊዜ ዉጤት ካላመጣ ጥረቱን ልታቆም እንደምትችል ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሯ አስታወቁ።
    続きを読む 一部表示
    12 分
  • የሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓም የዓለም ዜና
    2025/04/14
    የየካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና በኢትዮጵያ ለከተማ ልማት ሲባል የሚካሄደው የሰዎች መፈናቀል እንዲቆም አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ ። ሩስያ ትንናት ዩክሬን ሰሚ በተባለው ከተማ የጣለችው ጥቃት ዒላማ የዩክሬን ወታደሮች ነበሩ ስትል ዛሬ አስታወቀች። የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር ድብደባው ያነጣጠረው የዩክሬን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባ ላይ መሆኑን ጠቅሶ ኪቭ ሲቭሎችን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ በመጠቀም በከተማዋ ማዕከል ወታደራዊ ስብሰባ ማካሄዷን ኮንኗል። የጀርመን ፓርላማ ከሦስት ሳምንት በኋላ ፍሪድሪሽ ሜርስን በመራኄ መንግስትነት ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • የሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
    11 分
  • የሚያዝያ 8 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/16
    የኢትዮጵያ “የመምህራን የኅብረት ሥራ ባንክ” በ2018 ሥራ ሊጀምር እንደሚችል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ ፍንጭ ሰጡ። ሚኒስትሩ ከትምህርት የቀሩ 7.2 ሚሊዮን ተማሪዎች ጉዳይ በጣም ሊያሳስብ እንደሚገባ ተናግረዋል። አልሸባብ በማዕከላዊ ሶማሊያ አዳን ያባል የተባለች ወታደራዊ ማዕከል ላይ ጥቃት ከፈተ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል አዛዥ መሐመድ ሐምዳን ደጋሎ ትይዩ መንግሥት መመሥረታቸውን ይፋ አደረጉ። አሜሪካ በኤርትራ እና በደቡብ ሱዳን ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው። ዶናልድ ትራምፕ "ማስፈራራት እና ሥም ማጥፋት እንዲያቆሙ" ቻይና ጠየቀች። እስራኤል ወደ ጋዛ ሰብአዊ ርዳታ እንዳይገባ መከልከሏን እንደምትቀጥል አስታወቀች።
    続きを読む 一部表示
    13 分
  • DW Amharic የሚያዝያ 7 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/15
    በአማራ ክልል ከመንግሥት የሚዋጉ ታጣቂ ኃይሎች “ችግሮችን ለመፍታት ወደ ውይይት እንዲመጡ” የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ። በደቡብ ሱዳን እየተባባሰ በመጣው ግጭት ካለፈው መጋቢት ወዲህ ከ200 በላይ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ125,000 በላይ የሚገመቱ ሰዎች መፈናቀላቸውን የተመድ አስታወቀ። ሶማሊያ ከ56 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለምርጫ ድምጽ ሰጪዎችን መመዝገብ ጀመረች።በሱዳን አስገድዶ መድፈር እንደ ጦር ሥልት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ተባለ። እስራኤል በጋዛ ሠርጥ በሚገኘው የኩዌት የመስክ ሆፒታል ደጃፍ በፈጸመችው የአየር ጥቃት አንድ የሕክምና ባለሙያ ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ።
    続きを読む 一部表示
    11 分
  • DW Amharic የሚያዝያ 5 ቀን 2017 የዓለም ዜና
    2025/04/13
    ሩሲያ በሰሜናዊ ዩክሬን በምትገኘው ሱሚ የተባለች ከተማ ላይ በባልስቲክ ሚሳይል ዛሬ እሁድ ጠዋት በፈጸመችው ጥቃት ሁለት ሕጻናትን ጨምሮ በትንሹ 32 ሰዎች መገደላቸውን ዩክሬን አስታወቀች። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በ60 ሀገራት የሚገኙ 2,600 ሠራተኞቹን ሊቀንስ ነው። በጋዛ በሥራ ላይ ከሚገኙ ጥቂት ሆስፒታሎች አንዱ ዛሬ እሁድ በተፈጸመ የእስራኤል የአየር ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የጋዛ የሲቪል ጥበቃ ኤጀንሲ አስታወቀ። በፓሪስ ማራቶን ኢትዮጵያውያኑ በዳቱ ሒርጳ እና ደራ ዲዳ ተከታትለው በመግባት አሸነፉ።
    続きを読む 一部表示
    8 分